“ትረፊ” ያላት ነፍስ ?……ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋያመለጠው መንገደኛ አስገራሚ ታሪክ

እድለኛው አንቶኒዮስ ከዛሬው የአውሮፕላን አደጋ በስንፍናው ህይወቱን አድኗል ።

ቦሌ አየር ማረፍያ ዘግይቶ በመድረሱ ከጉዞው የተስተጏጎለው ግሪካዊ መንገደኛ ከሞት ተርፏል። ግሪካዊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኛ አንቶኒዬስ ማቭሮፕሎስ ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በኢትዮጵዯ አየር መንገድ ET 130 ለመሳፈር ሰሞኑን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።

መንገደኛው አንቶኒዮስ ታድያ ዛሬ ማለዳ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ተነስቶ መዳረሻውን ናይሮቢ ኬንያ ባደርገውና ከቦሌ ለበረራ ከተነሳ በስድስት ደቂቃዎች ከበረረ በሗላ ቢሾፍቱ በተከሰከሰው ቦይንግ 737 ET 130 አውሮፕላን ለመሳፈር ነበር ትኬት የቆረጠው።

 

አንቶንዮስ በረራው ባይሰረዝበትና ባይቀር ኖሮ በአውሮፕላኑ አደጋ ህይወታቸውን ካጡት 149 መንገደኞች አንዱ ይሆን ነበር። 150 ኛው ተሳፋሪ ለመሆን ነበር እቅዱ። ይሁን እንጂ ፈጣሪ ለአንቶኒዮስ የፈቀደለት ዕድሜ ከተቀሩት ኢቲ 130 ቦይንግ ጀት አውሮፕላን ተሳፍረው ህይወታቸውን ካጡት149 ጋር አልጻፋትም ነበር ። እድለኛው አንቶኒዮ ስ 149ኞቹ መንገደኞች ከተሳፈሩ በሗላ በሁለት ደቂቃ ዝግይቶ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ደርሰ።

የአየር መንገዱ ሰራተኞች በመዘግየቱ ምክያት ወደ ናይሮቢ መጓዝ እንደማይችል ከይቅርታ ጋር ይነግሩታል። እሱም በርተቶ ይለምናቸዋል። ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ የበረራ ዝግጅቱን አጠናቆ በሩ መዘጋቱን አርድተውት ይመልሱታል።

አንቶዮስም በሃዘን ድባብ ጉዞው በመሰረዙ ቁጣውን በመግለፁ የፀጥታ ሰራተኛ በማረጋጋት ይልቁንም በመዘግየቱና ከናይሮቢ በመቅረቱ ” ከ 149ኙ መንገደኞች በህይወት ለመትረፍ መቻሉን ሲነግረው አንትኒዮስ በድንጋጤ ወድያው በሃዘን ተውጦ እውነትም “እድለኛ ” መሆኑን በፌስ ቡኩ ላይ ደስታውን ከመሳፈርያ ትኬቱ ጋር ይፋ አድርጎታል።

“እንኳን እግዜር አተረፈህ “ብሎታል የፀታው ሰራተኛ። የአንቶኒዮም ቁጣ በቅፅበት ወደ ደስታና እንዲሁም ሃዘን ተለውጠ ፈጣሪውንም አመስግኖ በቀጣዩ በረራ ለመጓዝ ትኬቱን ወደ ማስተካከል ተመለሰ። ድብለቅለቅ ስሜት ,,,,,ከሞት የመትረፍና በአደጋው ለሞቱት ሌሎች ደግሞ ሃዘን የመዋጥ ድብልቅልቅ ስሜት,,,,,እንዲህ ነች ,,,ዝብርቅርቅ ላንዱ ሞት ,,,ለሌላው ህይወት ,,,,

“እድለኛ ነኝ ” ነው ያለው አንቶዮስም የፈረንሳይ ራዲዮ እንደዘገበው። በናይሮቢ በሚካሄድ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ቢወጥንም ለበረራው በሁለት ደቂቃ ብቻ ዘግይቶ በመድረሱ ከሞት የተረፈው እድለኛው አንቶኒ ዮስ ማርቮሎፖሉዩስ። እውነትም እደለኛ ,,,,ትረፊ,,,, ያላት ነፍስ

Leave a comment