በሕዝብ ስም መነገድ ነውር ነው !

የአንድ አገርን ሕዝብ በብሔር ወይም በተለያዩ ማንነቶች በመከፋፈል በስሙ መነገድ የዘመናችን ልሂቃን መለያ ከሆነ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ከልዩነቶቹ ይልቅ የጋራ እሴቶቹና መስተጋብሮቹ የሚያመዝኑት ይህ ሕዝብ፣ በተለያዩ መልክዓ ምድሮችና የአየር ፀባዮች ውስጥ ቢኖርም ዕጣ ፈንታው ግን አንድ ነው፡፡ ለዘመናት የተለያዩ ገዥዎች ቢፈራረቁበትም፣ የተለያዩ ባዕዳን ወራሪዎች ቢዘምቱበትም፣ ለማመን በሚያዳግት ሰቅጣጭ ድህነትና ኋላቀርነት መከራውን ቢያይም፣ የግፍና […]

Read More በሕዝብ ስም መነገድ ነውር ነው !

ጠቃሚ መረጃ;- የውጭ አገር መንጃ ፈቃድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ

የውጭ አገር መንጃ ፈቃድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች ኢትዪጵያ ውስጥ ማሽከርከር የሚፈልጉ ከሆነ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ባለው ስምምነት መሰረት በያዙት መንጃ ፈቃድ ይስተናገዳሉ፡፡ ይህንንም አገልግሎት ለማግኘት፡- 1.መንጃ ፈቃዱ የወጣበት አገር አልያም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሀገሩ ኢምባሲ የመንጃ ፈቃዱን ህጋዊነት፣ የመንጃ ፈቃዱን የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜና ሌሎችንም ጉዳዮች በተመለከተ ማረጋገጫ ይሰጥበታል፡፡ 2.ይህንን ሰነድ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር […]

Read More ጠቃሚ መረጃ;- የውጭ አገር መንጃ ፈቃድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ

ሃምሳ በመቶ የሚሆኑ ፓስፖርቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ አለመሆናቸው ተገለጸ:- ሪፖርተር

በየዓመቱ ከሚታተሙ ፓስፖርቶች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ለኪሳራ እንደሚዳረጉ ኢሚግሬሽን አስታወቀ፡፡ ማኅበረሰቡ ፓስፖርቱን በአግባቡ እንደማይዝ፣ እንደ ቀበሌ መታወቂያ የሚገለገሉበት ሰዎች መኖራቸው፣ እንዲሁም ጠፋብን በሚል ሰበብ በአንድ ዓመት ውስጥ ደጋግመው ፓስፖርት የሚያወጡ ግለሰቦች በርካቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች 50 በመቶ ያህል ፓስፖርቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እንደማይውሉ ለሪፖርተር የገለጹት፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ ምክትል ዋና ዳይሬክተር […]

Read More ሃምሳ በመቶ የሚሆኑ ፓስፖርቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ አለመሆናቸው ተገለጸ:- ሪፖርተር

ፖሊስ፦በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ

ፖሊስ በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር አገኘሁ አለ። ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ የጅምላ መቃብሮቹ የ200 ሰዎች አስክሬን ይዘዋል። ፖሊስ ይህን ያለው የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሐመድ ዑመር በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ትናንት በቀረቡብት ወቅት ነበር። ፖሊስ ጨምሮም የሟቾችን ማንነት ለማጣራት እየሰራ መሆኑ ተናግሯል። አምነስቲ ኢንትርናሽናል የሶማሌ ክልል […]

Read More ፖሊስ፦በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ

በህጋዊ ሽፋን ህገወጥ የሥራ ጉዞ ከሰኞ ጀምሮ ይታገዳል

የሥራ ስምሪት ባልተፈቀደባቸው በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ህጋዊ በሚመስል መንገድ ለሥራ እየተጓዙ የሚገኙ ዜጎችን ከሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ለመታደግ ከጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የማገድ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተቋቋመው ሀገር አቀፍ ግብረ ኃይል ትናንት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት በሚኒስቴሩ የውጭ […]

Read More በህጋዊ ሽፋን ህገወጥ የሥራ ጉዞ ከሰኞ ጀምሮ ይታገዳል