ቤታችን ውስጥ ምን እየሰራን እንቀመጥ?

ልክ ንስር ራሷን ለይታ እንደምታድስ…እኛም ይሄንን ጊዜ ራሳችንን እናድስ ህይወታችንን እንገምግም. ..ያለፈ እድሜያችንን ያለፈ ህይወታችንን በመቃኘት ራሳችንን ላይ እንስራ

እነሆ እኔም በሚያመቸኝ መንገድ አስተካክዬ ህይወቴ ላድስበት በቤቴ ውስጥ ለመቀመጥ ወሰንኩ
ባይለምድብኝም ዛሬ በቤት የመቆየት ፩ኛ ቀን ላይ ነኝ። እቤት እንቆይ ወገንን እንጠብቅ በሚለው መርህ መሰረት።
በቆይታዬ ይህንን አቅጃለሁ ይጠቅማል ብዬ ስላሰብኩኝ ልክ እንደመምህሬ ዳናውን በመከተል እና በመኮረጅ ለራሴ እንዲሁን አርጌ ልተገብረው ወሰንኩና ላካፍላችሁ ወደድኩ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግብ
መልካም የሰውነት፣ የህሊና፣ እና የመንፈሳዊ ጥንካሬና ጥምረትን ማሳካት። ጤነኛነት። የፈጣሪን መልዕክት መገንዘብና ለእርሱ ታዛዥ መሆን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግልፅ የምናብ ግብር
በየቦታው ጤናማ፣ በፍቅር የተሞላ፣ ሰላማዊ፣ የሚተባበር፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው፣ ደስተኛ እና በምስጋና የተሞላ ህይወት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተግባራት

  1. መንፈሳዊ
    በምስጋና የተሞላ ፆም፣ ፀሎት
    -መንፈሳዊ ትምህርቶች መስማት
    -መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ
    -መንፈሳዊ ቪዲዮ እና መፅሀፍ ማንበብ
    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
  2. ህሊና
    መፅሀፍ ማንበብ
  • ልምድ ልውውጥ ግዜ/የትምህርት ጊዜ
    ኦንላይን የግል ስብእና ስልጠና መውሰድ
  • ግልፅ የምናብ ግብን ማየት
    ሀያ ስላለን ነገር ምስጋናን ሀያ ስለምንሻው ነገር ምስጋናን መፃፍ።
    ኦንላይን መማር ቪዲዪ ማየት
    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
  1. ሰውነት

ፊልም
ውሀ መጠጣት
ምግብ ማብሰልና ማፅዳት
ናፕ ማድረግ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

  1. ማህበራዊ
    ለቤተሰብ፣ ጋደኞች፣ ዘመድ፣ ጎረቤት በስልክ ፍቅርን አክብሮትን ምስጋናን መግለፅ።
    የቤት መልካም ውሎአችንን ማካፈል።
    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
  2. ራዕይ መክሊት
    ስልጠና ማንዋል ማዘጋጀት
    መፅሀፍ መፃፍ
    ፕሮፖዛሎቼን መጨረስ
    እቅድ መገምገምና ማስተካከል
    የጀመርኳቸውን ስራዎች መጨረስ
    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
  3. ገቢ
    ኦንላይን ስልጠና ማርኬት መስራት
    ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
    የማይደረጉ
    ሚድያ አለማየትና ማዳመጥ።
    በቀን አንድ ግዜ ብቻ ዜና ማየት።
    ስለፍርሀትና ጭንቀት አለማውራት፣ አለማሰብ።
    ስለ ተስፋ እና ጤንነት ማሰብና ማውራት።
    ከቤት አለመውጣት
    ፊትንም ሆነ ሰዎችን እኛ ለመንካት
    ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
    መደረግ ያለበት
  4. በቀን አስር ግዜ እጅን መታጠብ
  5. ከላይ የተጠቀሱትን ማድረግ
  6. በምስጋና እና ደስተኛ ስሜት ውስጥ መቆየት።
  7. በግርግዳ ላይ ይህንን ለጥፎ በቀን ውስጥ ደጋግሞ እያዩ መከተል።
    ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
    አስታውሱ
    ይሄ እድል ነው ራሳችንን የምናድስበት እድል …..
    ከግርግሩ ወጥተን ራሳችንን እንመልከት ህይወታችንን እንቃኝ
    ሰላም ሁኑልኝ። #ሀና_ሀይሉ

Leave a comment